የኮሪደር ልማት ላይ በከብቶቻቸው ጉዳት ያደረሱ ሰዎች ተቀጡ


ከይር ዜና:- በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ክልል ውስጥ የኮሪደር ልማት ላይ ጉዳት 13 ከብቶች ጉዳት ያደረሱ ሲሆን የከብቶቹ ባለቤቶች መቀጮ ተጥሎባቸዋል። እንስሳቶቹ በልማት ስራው ላይ ጉዳት በማድረሳቸው ምክንያት የእያንዳንዱ ከብት ባለቤት አምስት ሺህ ብር፣ በድምሩ ስድሳ አምስት ሺህ ብር እንዲከፍሉ ዛሬ ተወስኗል።

የወረዳው ደንብ አስከባሪ ክፍል እንዳስታወቀው፣ በልማት ስራዎች ላይ በቸልተኝነት ጉዳት እንዳይደርስ ማህበረሰቡ ከዚህ አይነት ተግባር እንዲታቀብ ጥሪ አቅርቧል።