ከይር ዜና:- ከዚህ ቀደም ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የጀመረችው የጣናነሽ-2 ጀልባ ለአንድ ወር ተኩል ያህል ተጉዛ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጣለች።
በጉዞ ወቅት ያጋጠመውን አስቸጋሪ የመንገድ ሁኔታ ለመፍታት የተለያዩ የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመንግስት አካላት ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል፡፡
በዚህም የጣናነሽ-2 ጀልባ ከሰዓታት በፊት የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጣ ደወሌ መግባቷን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡