የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2017 ትምህርት ዘመን በበይነ መረብ ለሚፈተኑ ተፈታኞች ሞዴል ፈተና በሚከተለው መርሃ ግብር መሠረት አዘጋጅቷል፡፡ ፈተናው ዛሬ መሰጠት የጀመረ ሲሆን የትምህርት አመራርና መምህራን እንዲሁም ሁሉም የባለድርሻ አካላት የተሳካ የሞዴል ፈተና እንዲኖርና በሂደቱም ተፈታኞቻችን ከሲሰተሙና ከፈተና ማዕከላቱ ጋር በአግባቡ እንዲተዋወቁ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በቂ ልምምድ በራስ መተማመንን ለማዳበር ይጠቅማል፡፡
የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል!!