ካርዲናል ሮበርት ፕሪቮስት 267ኛው የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት መሆናቸው ታውቋል።
ካርዲናል ሮበርት ፕሪቮስት ቺካጎ የተወለዱ የ69 ዓመት ካርዲናል ሲሆኑ፣ ከሰሜን አሜሪካ የመጀመሪያ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
ካርዲናሉ ስማቸውም ሊዮ 14ኛ ተብሎ ተሰይሟል፡፡
ከ40 ሺህ በላይ ምዕመናን ሁነቱን ለመከታተል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መገኘታቸውን የፖሊስ መረጃን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡት ምዕመናንም ደስታቸውን እየገለፁ ናቸው፡፡
ሁለተኛው ዙር ምርጫ አለመሳካቱን የተመለከቱ ምዕመናን ምርጫው ለነገ ይተላለፋል ብለው ቢጠብቁም ምርጫው በአጭሩ በመጠናቀቁ ደስተኞች መሆናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡
በካርዲናሎች ምርጫ ሁለት ሦስተኛውን ድምጽ ያገኙት አዲሱ ርዕሰ ሊቃለ ጳጳሳት ማንነት ከደቂቃዎች በኋላ እንደሚገለጽም ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ካርዲናል አባ ብርሃነ ኢየሱስን ጨምሮ 133 ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ካርዲናሎች በምርጫው ላይ መሳተፋቸው ታወቋል፡፡