"መርከቧን በሰላም ለማሳለፍ ሀይል ይቋረጣል'' የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት

ወደ ሃገር ውስጥ በመግባት ላይ የምተገኘውን ጣና ነሽ መርከብ ለማሳለፍ ሲባል የሃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት አስታወቀ።

የኤሌክትሪክ ሀይሉ የሚቋረጠው የመርከቧ ከፍታ ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስታንዳርድ በላይ በመሆኑ ዋና አስፖልት ተሻጋሪ የመካከለኛ እና ዝቅተኛ መስመሮች አደጋ እንዳያደርሱ እና መርከቧን በሰላም ለማሳለፍ ሲባል ነው ተብሏል።

በዚህም ከነገ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ መርከቧን በተሸከመው ተሽከርካሪ ፍጥነት እና የትራፊክ ፍሰት ለሚወሰን ጊዜ  በሠመራ፣ አይሳኢታ፣ ሎግያ፣ ሚሌ እና ኤሊውሃ አካባቢያቸው የሃይል አቅርቦት ተቋርጦ እንደሚቆይ አገልግሎቱ አስታውቋል። 

ስለሆነም በአካባቢው የሚገኙ ደንበኞች መርከቧ በሰላም አልፋ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።