አቶ አህመድ ሺዴ የፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ነገ ይፋ ሊያደርጉ ነው
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 35ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማክሰኞ ሰኔ 03 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ም/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሂዳል፡፡
በስብሰባውም የም/ቤቱን 4ኛ አመት የስራ ዘመን 34ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ተመርምሮ እንደሚጸድቅና የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት በተመለከተ በሚያቀርቡት የበጀት መግለጫ (Budget Speech) ላይ በመወያየት ረቂቅ የበጀት አዋጁን ለዝርዝር እይታ ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራት መሆናቸውን ምክር ቤቱ ለመናኸሪያ ሬዲዮ በላከው መግለጫ ተመላክቷል፡፡